የዲጅታል ቴክኖሎጅ አሰራርን ለማዘመን፣ ቀልጣፋ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት፣ ትርፋማ ለመሆን፣ በጣም ወሳኝነት ያለው ነው ዘመናች የዲጅታል ቴክኖሎጅ ዘመን እንደመሆኑ መጠን አሰራራችን በዲጅታል ቴክኖሎጅ ካልታገዘ ተቋማት ለብዙ የገንዘብ ወጭ ፣ የጉልበትና የጊዜ ብክነት እንዲደርስባቸው ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ተቋማቶች ከሌሎች ተቋማቶች አሰራራቸውን ዲጅታል በማድረግ ቀልጣፋና ምቹ የዲጅታል ቴክኖሎጅ በመዘርጋት ራሳቸውን ተወዳዳሪ በማድረግ በልጠው መገኘት አለባቸው፡፡
በመሆኑም ድርጅታችን ለብዙ የግልና የመንግስት ድርጅቶችን የአሰራር ችግሮችን በመለየት በሀገራችን ያለውን አለም የደረሰበትን የዲጅታል ቴክኖሎጂን አጠቃቀም ሀገራችንና ማህበረሰባችን እንዲጠቀሙበት በማድረግ ስራን፣ አሰራርን ቀላል፣ ቀልጣፋና ምቹ እንዲሆን የማድረግን ስራ እየሰራን እንገኛለን። አለማችን አሁን ላይ የአኗኗር ዘይቤውን ቀላል እንዲሆን ካደረጉት አንዱ የዲጅታል ስርአት ከመጣ በኋላ ቀለል ባለ መልኩ ሰው አኗኗሩን ቀላል እንዲሆንለት አድርጓል። በእያንዳንዱ የማህበረሰብ፣ የመንግስትና የግል ተቋማት ላይ ብዙ ስራዎች አሰልች፣ አድካሚ፣ ብዙ ገንዘብ፣ ብዙ ግዜ፣ ብዙ የሰው ሀይል የሚጠይቅ ስራና አሰራር ያለበት ሲሆን ይህንን አሰራርና ስራ በቅልጥፍና፣ በታማኝነት፣ ከብዙ ግዜ ወሳጅነት፣ ከብዙ ወጭ የሚገላግለው አሰራርን በማዘመን ዲጅታላይዜሽን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ለአንድ ተቋም ወሳኙ የሰው ሀብት ሲሆን ተቋሙ ትርፋማ እንዲሆን የሚያደርግ፣ አንድን ተቋም እንዲከስር የሚያደርግ፣ አንድን ተቋም ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርስ የሚያደርግ ውጤታማ የሚያደርግ፣ አንድን ተቋም ህልውና የሚወስነው የተቋሙ የሰው ሀብት አስተዳደር ነው።
በመሆኑም የአንድ ተቋም የሰው ሀብትን በደንብ በዲጅታል የቁጥጥር ስርአት በመዘርጋት፣ በዲጅታል የሰው ሀብትን መረጃ በመያዝ በአግባቡ ከተመራና በዲጅታል የቁጥጥር ስርአት ውሰጥ በማስገባት ማን በአግባቡ በስራ ገበታው በተቋሙ ውስጥ በመገኘት ስራውን ማከናወኑን፣ የተሰጠውን ተግባር በአግባቡ መስራቱን የምንቆጣጠርበት የሰው ሀብት በሰውና በወረቀት አሰራር ከሆነ በጣም አድካሚ፣ አሰልች የሚሆን ሲሆን ሁሉም ተቋማት ወደ ዲጅታሉ አለም በማሸጋገር የሰው ሀብት ቁጥጥር ስርአቱን ማዘመንና የሰው ሀብት አያያዝ ስርአታችንን ቀላል፣ ቀልጣፋና ምቹ በማድረግ ስራን መስራት ያስችለናል።
የሰው ሀብት አስተዳደር የመረጃ አስተዳደር ስርአት ማለት አሁን ላይ የመረጃ አያያዝ ስርአቱ ከወረቀት የመረጃ አያያዝ ስርአት ወጣ ባለ መልኩ ቀላልና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ የአንድን ተቋም የመረጃ አያያዝ ስርአቱን ዲጅታላይዝ የማድረግ ስርአት ነው። የአንድ ተቋም የሰው ሀይል መረጃ በቋሚነት ከእሳት፣ ከጎርፍ አደጋዎች ለመከላከል፣ ከመረጃ ስርቆት፣ ከመረጃ መቀደድ፣ ከመረጃ መጥፋት ለመከላከል ዋነኛ መፍትሄ የሚሆነው ዲጅታላዜሽን በተቋማችን ስንዘረጋ ይሆናል ማለት ነው።
የተቋማችን ሰራተኞች የፈለጉትን የግለሰብ መረጃ ቢጠይቁ በቅጽበት ማግኘት የሚያስችል ሲሆን የተቋማችን ሰራተኞች በአንድ ግዜ የጠየቁትን መረጃ አግኝተው ወቅታዊ መረጃ በማግኘት መስተናገድ ያስችላቸዋል። በአንድ ተቋም የሰራተኞች የቁጥጥር ሰርአት መኖር ያለበት ሲሆን ይህንን ለማድረግ በዲጅታል ቢደገፍ በጣም ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል ሲሆን ለተቋም ውጤታማነት ከፍትኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።